ሥር ነቀል የወጣቶች የባህል ለውጥ በታየባት ኢትዮጵያ፣ ስኬትቦርዲንግ በግል እና በጋራ መተንፈሻነት ትልቅ ሥፍራ እየያዘ መጥቷል። እ.ኤ.አ በ2013፣ ኢትዮጵያ ስኬት የተባለው ማኅበር መመሥረቱ፣ ሀገሪቱ የመጀመሪያውን የተደራጀ የስኬትቦርዲንግ ማኅበረሰብ እንዲኖራት አደረገ። ከዚያም እ.ኤ.አ በ2016፣ የሀገሪቱ የመጀመሪያው እና ብቸኛው ከክፍያ ነጻ የሕዝብ ፓርክ አዲስ ስኬት ፓርክ ተከፈተ። እነዚህ ትላልቅ ኹነቶች ስኬትቦርዲንግ እንደ ስፖርት ብቻ ሳይሆን እንደ ባህላዊ የነጻነት መግለጫ መሳሪያ የሚታይበት ሰፊ ንቅናቄ መጀመሩን ያመለክታሉ።

የዚህ ስፖርት ዕውቅና እያደገ ቢመጣም፣ ሴቶች እንዳይሳተፉ ከፍተኛ እንቅፋቶች ይገጥሟቸው ነበር። የሚደርሱባቸውን ዘለፋዎች እና ትንኮሳዎች ለመከላከል፣ ኹለት ሴት ስኬተሮች እኤአ በ2020 ኢትዮጵያን ገርል ስኬተርስ የተባለ ማኅበር መሠረቱ። ይህ ማኅበር ልጃገረዶች እና ሴቶች ስኬትቦርዲንግ የሚለማመዱባቸውን አስተማማኝ ሥፍራዎች ለመፍጠር ያለመ ነው። ተልእኮውም ግልፅ ነበር፦ «ለሴት ልጆች ነጻ የስኬትቦርዲንግ ትምህርት መስጠት።» ከጽንሰቱ ጀምሮ፣ በዋነኝነት ዕድሜያቸው ከ10-25 ዓመት ያሉ 150 አባላት ማሰባሰብ ከመቻሉም በላይ፤ የትግል፣ የእኅትማማችነት እና የማብቃት ምልክት መሆን ችሏል። በየሳምንቱ ቅዳሜ ጠዋት፣ አዲስ ስኬት ፓርክ በተለየ ሁኔታ ሴት ልጆች ብቻ ይማሩብታል፣ ይለማመዱበታል፣ እንዲሁም እኅትማማችነትን ይገነቡበታል፤ይህ ደግሞ በአብዛኛው ሴቶችን ለመገደብ በሚሞክር ማኅበረሰብ ውስጥ ነጻ የመውጣት ተግባር ነው። የኢትዮጵያዊት ሴት ስኬተሮች ስብስብ በስኬትቦርዲንግ አማካይነት ለነጻነት ዐዲስ ትርጉም በመስጠት፣ ነጻ ሥፍራን እንዴት መፍጠር እንደሚቻል በምሳሌነት ያሳያል። ስብስቡ የራሱን ትርክት ፈጥሮ፤ ወጣት ሴቶች የራሳቸው ገላ፣ ማንነት እና ድምጽ ባለቤትነታቸውን የሚያስመልሱበትን ዕድል ይሰጣቸዋል። ማኅበሩ የጨዋታ ቦታ ከመሆን ባለፈ፣ እንደ ጉልሕ ማኅበራዊ እንቅስቃሴ፣ እንደ የመላቀቅና የዐርነትለዋጭ እርምጃም ያገለግላል።

Hanna Leka, the girls, 2024, Photography, 11” × 14”

ስኬት፣ ፈጠራ፣ ነጻነት የተሰኘው ዐውደ ርእይ በፎቶግራፍ ጥበብ፣ በሥዕል፣ በኮላዥ፣ በኦዲዮ እና በዘጋቢ ፊልም ጥበባት የተሰማሩ ዐምስት ሴት ከያንያንን በአንድ ያስተባበረ ነው። ዐውደ ርእዩ ሴትነት፣ ፈጠራ፣ ትግል እና ጨዋታ እንደምን ተገናኝተው ሴቶች እና ልጃገረዶች ራሳቸውን ማየትና ማረጋገጥ የሚችሉበትን ሥፍራ ለመፍጠር እንደሚያስችሏቸውይፈትሻል። የዐውደ ርእዩ ራዕይ የመነጨው ኢትዮጵያውያት ልጃገረዶች፣ በሌሎች ቦታዎች እንዳሉት ልጃገረዶች ሁሉ፣ ለመኖር፣ ለመፍጠር ወይም በነጻነት ለመንቀሳቀስ ፈቃድ እንደማይጠብቁ ከማየት ነው። ይልቁንም ሥፍራቸውንእየተቀበሉ፣ ቅርፅ እየሰጡት እና እንደገና በራሳቸው መልክ እየቀረፁት ነው። ዐውደ ርእዩ ይህን በስኬትቦርድ ወይም በሸራ ላይ፣ ወይም በሌላ ክዋኔ የሚገለጽ ራስን የመበየን ተግባር እንደ ወሳኝ የመተንፈሻ መንገድ ያከብረዋል። ነጻ መውጣት በአንድምልክት ብቻ ሳይሆን፤ በተለያዩ የሚታዩ፣ ተዛምዷዊ፣ ውስጥ ተመልካች፣ ንብርብር፣ እና ሥነ ሥርዓታዊ ተግባራት ሕብርይገለጻል። በጥልቅ ስሜት ገላጭ ፎቶግራፎች፣ ሻካልሴባላቸውኮላዦች፣ በመሳጭ የድምፅ ልምምዶች እና የስኬተር ልጃገረዶችን የተግባር እንቅስቃሴዎች በሚያሳዩ ዘጋቢትዕይንቶች አማካይነት ዐውደ ርእዩ ነጻ ሥፍራ መፍጠር ከድፍረት እና ከእንቅስቃሴ ጋር የመያያዙን ያህል፤ በመተሳሰብ፣ በመተያየት እና በእርስ በርስ ግንኙነት እንደሚገለጽ ያሳያል።

Hanna Leka, Skating with Netela, 2024, Photography , 11” × 14”

የሐና ለካ የኢትዮጵያ ሴት ስኬተሮች የፎቶግራፍ ስብስብ ለዐውደ ርእዩ ጠንካራ መንፈስ መሠረት ነው። በዐውደ ርእዩላይ በቀረቡት ፎቶግራፎቿ፣ ፍጥነታቸውን፣ ኮንክሪት ላይየሚንካኩ ስኬትቦርዶችን፣ በዝላዮቻቸው መኻል የተውለበለቡሹሩባዎቻቸውን፣ እንዲሁም ሚዛን የመጠበቅና የመውደቃቸውን ጥልቅ ስሜት በተፈጥሮ ብርሃን ብቻበየተፈጥሯዊ አጋጣሚው አጉልታ ታሳያለች። ፎቶግራፎቹ ጥሬ እና ያልተነካኩ ሆነው ስኬተሮቹን ሕያው የሚያስመስሉ ናቸው። ሐና ወጣት ሴቶቹ ጎዳናዎችን፣ መሸጋገሪያዎችን እና ባዶ ቦታዎችን ወርሰው ከተማዋን ወደ ራሳቸው የመጫወቻ ሥፍራነት እየቀየሯት እንደሆነ ታሳያለች። በሥራዎቿ ላይ ዐመፅ ቡረቃን ይመስላል፤ ተቃውሞ የሣቅ ያህል ይሰማል፤ እና ሥር ነቀል ፖለቲካም በጨዋታ ይገለጣል። ከፎቶግራፎቿ ጋር በኢትዮጵያ ሴት ስኬተሮች የተሠሩ ዚኖች (መጽሔቶች)ተካተዋል። ከማኅደር ምስሎች፣ ስኬቾች እና መግለጫዎች የተውጣጡ እነዚህ ስብስብ ሥራዎች፣ እንደ ታሪክም እንደ አዋጅም ሆነው፤ የመንቀሳቀስ፣ የመታየት እና ራስን የመግለጽ መብታቸውን አጥብቀው የሚጠይቁ ልጃገረዶችን ድምጾችአጉልተው ያሰማሉ።

Medina Mohammed, Nejuma’s house, Photography, 5” × 7”

የመዲና መሀመድ ሥራ የቤተሰብ አልበምን የሚያስታውስ ቅርበት ተመልካቿ ላይ ይፈጥራል፤ ፎቶግራፎቿ ጓደኝነት፣ መተሳሰብ እና የዕለት ተዕለት ኑሮን በምስል ቀርጸዋል። ከተለመደው አቀራረብ በተለየ፣ ሥፍራዋን እንደ ትውስታ ግድግዳ በመጠቀሟ፣ ወደ ሥራዎቿ የተጠጋ ሁሉ ወደ ግል መኖሪያ ቤት የገባ ያህል ስሜት ይሰማዋል። አደራደሯ በዕለትተዕለቱ እና በሃይማኖታዊው ኪነ ውበት ላይ የተመሠረተ መሆኑ፣ ፎቶግራፎቹ ንብርብር ትርጉም እንዳላቸው፣ ጥልቅ ስሜቶችን እንደተሸከሙ ሕብረ ከዋክብት እንዲታዩአስችሏቸዋል። ሥራዎቹ ተሸምነው የቀረቡባቸው የመቅደስመሰል ዝርዝር ገጽታዎች፣ ሕዝባዊ ዐውደ ርእይን እና የቤትክዋኔን ልዩነት ወደሚያደበዝዝ ሥፍራ ተመልካቾችን ይጋብዛሉ። ከዚህ የሚወለደው ትውስታ እና መተሳሰብንየሚያከብር ከባቢ የዕለት ተዕለት ሕይወትን የትግል እና የነጻነት ሥፍራነት ያረጋግጣል።

Mulu Legesse, Balancing, 2025, Acrylic on canvas, 45.3” × 54.7”

ሙሉ ለገሰ ከአካላዊ ዐመፅ ይልቅ ውስጣዊ ጥንካሬንታጎላለች። ስኬትቦርዲንግ በራሱ የሕዝብ ድምጽ ማሰሚያቢሆንም፤ ሙሉ ከስኬቾች እና ከቁርጥራጮች የሠራችውንብርብር ኮላዥ ኢ-ቀጥተኛ፣ ዑደታዊ እና ጥልቅ የዕድገትኺደትን ያንጸባርቃል። ትላልቆቹ የአክሬሊክ ሥዕሎቿ ሚዛናዊነት፣ ሰላም እና ጥንካሬ ፍለጋን እያሳዩ፤ ውስጣዊ ማንነትን ደግሞ የራሱ ወሳኝ ሥፍራ ያደርጉታል። ሙሉ ምሉዕነትን በማጉላት እና የእናትነትን እና የከያኒነትንተደጋጋፊነት በማሳየት፤ ነጻነትን ከሕዝባዊ ጥያቄነት ባሻገር፣ግላዊ ሙሉነትንም እንዲያካትት ታሰፋዋለች።

Tsion Haileselassie, Reflection of oneself, 2021, photography, 11” × 14”

የጽዮን ኃይለ ሥላሴ የፎቶግራፍ ሥራ ጸጥ ያለ፣ ግን ደግሞየታመቀ ኃይል ያለውን ኑባሬ ያስተዋውቃል። ምስለ ሰብፎቶግራፎቿ (ፖርትሬቶቿ) በመረጋጋት፣ በትኩረት እና ሆን ብሎ በመታየት ተግባር ራሳቸውን ይገልጻሉ። እያንዳንዱ ምስል የተቀናበረበት የተጠና ብርሃን እና ጥላ ፊት፣ አካል ወይም ማየትላይ ያተኩራል። ሥራዋ በመረጋጋት ራስን ማግኘትን በማጉላት፤የንቁ አተኩሮን፣ የጽብረቃን እና ራስን የመገንዘብን ሥር ነቀልነት በማሳየት፤ ተመልካቾች ተጋላጭነትን እንደ ጥንካሬምእንዲመለከቱት ይጋብዛል።

የኢሪ ዲ ‘ሪክላሜሽን ቼምበር’ በድምፅ፣ በንዝረት እና በክዋኔመገናኛ ላይ ያለ መሳጭ የስሜት ሕዋሳት ተሞክሮ ነው። ተሳታፊዎች በኦርጂናል በድምፃዊቷ የድምፅ ቅንብሮች እየተመሩ፣ ከራሳቸው ጋር እንዲገናኙበት ታስቦ ከድምፅወደታነጸው የሐር ትል ጎጆ መሳይ ጨለማ የማምለጫ ሥፍራይገባሉ። ተሳታፊዎች በምኞት ካርድ ጀምረው፣ በጽብረቃ ካርድ በመጨረስ፤ ኑባሬን፣ ተጋላጭነትን እና ከራስን መገናኘትን በሚያጎላ ግላዊ እና መሳጭ መስተጋብር ውስጥ ይሳተፋሉ። ይህ እልፍኝ ዐውደ ርእዩን ከዕይታዊ ማሳያነት ውስጣዊ ኑባሬን፣ ትውስታን እና የራስ የሆነውን ማስመለስን ወደ ማንጸባረቂያነትይቀይረዋል።

Medina Mohammed, shirube, Photography, 5” × 7”

ዐውደ ርእዩ በተለያዩት ሥራዎች መኻል ውይይት ይፈጥራል፤እያንዳንዱ ሥራ ሌላውን እንዲያጎላ በማድረግ ጎብኚዎችን ከሕዝባዊው ትዕይንት ወደ ራሳቸው ጠልቀው እንዲገቡይመራቸዋል። ትዕይንቱ በሚታይ፣ የጋራ የነጻነት መግለጫ ይጀምርና፤ የመሆንን የተደበቀ ጉልበት ለመግለጥተመልካቾችን ቀስ በቀስ ወደ ውስጥ ይስባቸዋል። በመግቢያው ላይ፣ የሐና ለካ ፎቶግራፎች፣ ስኬትቦርዶች እና ዚኖች ደማቅ ሕዝባዊ ደስታን ይዘክራሉ። ከሐና ፎቶግራፎች ትይዩ፣ የመዲና መሀመድ የትውስታ ግድግዳ ነጻነትን በመተሳሰብ ድርጊያዎች፣ በሥርዓቶች እና በማኅበረሰብ ክዋኔዎች ያሳያል። ጎብኚዎች ወደ ውስጥ ዘልቀው ሲገቡ፣ግላዊ የማደግ ትግሎች ያጋጥሟቸዋል፦ የሙሉ ለገሰ ትላልቅ ኮላዦች ድርድርን፣ ሙሉነትን እና ፈጠራን ሲያንጸባርቁ፤የጽዮን ኃይለ ሥላሴ ቅሩብ ምስለ ሰቦች ደግሞ ጸጥ ያሉ አፍታዎችን በመስጠት ተጋላጭነትን እና የሴትነትን ውስብስብጥልቀት ያሳያሉ። በመጨረሻም ጎብኚዎች የኢሪ ዲ የድምፅ እልፍኝ ውስጥ በመግባት፤ በድምፅ ንዝረት እና ክዋኔዎችእየተመሩ ከራሳቸው ጋር ይገናኛሉ። ይህ ጕዞ በመኖር የተገኙተሞክሮዎችን የሚያንጸባርቅ ሆኖ፤ ከሚታየው ገጽ፣ በጋራትውስታ እና በግል ማንነት በኩል፣ ወደ ውስጣዊ ማንነትየሚመራ እና ራስን በማየት ትዕምርታዊ ክዋኔ የሚጠናቀቅአርኪኦሎጂያዊ ጕዞ ነው።

Hanna Leka, Semhal, 2024, Photography, 11” x 14

ድፍረት፣ ፈጠራ እና ብሩህነት መመስከራቸው በራሱ ለውጥ አምጪ መሆኑን ያረጋግጣል። ነጻነት በብዙ መልኩ ይገለጣል፦ በሐና ለካ በኩልሕዝባዊ እና ጨዋታ ሆኖ፣ በመዲና መሀመድ ተዛምዷዊነትንተላብሶ፣ በጽዮን ኃይለ ሥላሴ በውስጥ ተመልካችነቱ፣ በሙሉ ለገሰ በኩል በንብርብራዊነቱ እና በኢሪ ዲ ደግሞ ሥርዓታዊ ሆኖ ተገልጿል። ዐውደ ርእዩ በጋራ ሆነው የነጻነት ሥፍራንየሚፈጥሩትን ያልታዩትን ልፋቶች፣ የግል ትግሎች እና ሕዝባዊ ተግባራትን አጉልቶ በማሳየት፤ መፍጠር ማለት መታገል፣ መጫወት ማለት መቃወም፣ እና ሕብረትም ዓለምን የመለወጥ ተግባር መሆኑን ያስታውሰናል። ከትርዒቱ ባሻገር፣ ዐውደ ርእዩየበዓል፣ የመተዋወቂያ እና የመደናነቂያ መድረክ ነው፦ አሁንበዚህ ተገኝተን፣ እርስ በርሳችን እየተያየን፣ አብረን የወደፊቱን እየገነባን ነው።

Layla Yamamoto, Refracted Sunlight 2 (Article 213), Acrylic on canvas, 80cm diamater (round)

オープンコール展示
© apexart 2025

展示ページへ